እግዚአብሔር ብቻውን ሁሉን ሊያደርግ የሚችል አምላክ ስለሆን እርሱ አሻግራለሁ ካለ ለማሻገር የማናችንንም ድጋፍ አይፈልግም፣ በህይወት ማዕበልና ወጀብ ብዛት እምነታችን እየተፈተነ ሊሆን ይችላል ግን በድካማችንም ቢሆን ወደ እርሱ ስንጮህ ነፋሳት ማዕበሉና ውጀቡ ለቃሉ የሚታዘዙለት ጌታ ማዕበልና ወጀቡን ጸጥ ያደርገዋል፣ የጠራን አምላክ የሚያደርስ እንጂ መንገድ ላይ የሚተው እባት ስላልሆነ እርሱ ከያዘን በምንም አይነት ማዕበል ውስጥ ካለመናወጥ እናልፋለን፣ እምነታችንን በእርሱ ላይ ካደረግን ደግሞ ምንም የሚጥለን ነገር አይኖርም፣
view more