የቤተክርስቲያን መልክ በውስጥና በውጭ የሚገለጥ ነው:: በውስጥ በሰላም የተሞላች ነበረች:: በውጭ ደግሞ መፈራትና ሞገስ ነበራት:: የቤተክርስቲያን ሰላም ከጌታ የተቀወለችው በውጭ ባለው ሁኔታ የማይወሰን በበመከራና በፈተና ውስጥ እንኳ የማይደፈርስ የፀና ሰላም ነው::
ጌተ የሰጠን ሰላም አለም እንደሚሰጥ ሳይሆን በሁኔታዎች የማይደፈርስ የውስጥ ሰላም ነው:: እያንዳዳችን በዚህ ሰላም ከተሞላን ደግሞም ከጠበቅነው ቤተክርስቲያንም በዚሁ ሰላም የተሞላች ትሆናለች:: ስለዚህ በቤታችን በስራ ቦታ በስፍራው ሁሉ ራስን በመግዛት ጌታንም በመታመን የሰላም ሰው ሆነን ልንመላለስ ያስፈልጋል::
view more