የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ የእግዚአብሔርን በጎነት መናገር፣ መንፈሳዊ ቤት ሆኖ መሰራትና መንፈሳዊ መስዋዕትን ማቅረብ ነው፣ ታላቁ ትዕዛዝ ደግሞ አምላካችንን በፍጹም ልባችን ነፍሳችንና ሃሳባችን መውደድና ባልንጀራችንን ደግሞ እንደራሳችን መውደድ ነው፣ ጌታን መውደዳችንን የመንገልጸው ከአላማው ጋር በመተባበርና ለቃሉ በመታዘዝ ሲሆን በምድር ሲያስቀምጠን ትልቁ አላማው ደግሞ ወንጌልን ለፍጥረት ማድረስ ነው፣ ባልንጀራችንን እንደራሳችን እድርገን መውደዳችንን የምንገልፀው ለባልንጀራችን መልካም ነገርን በማድረግ ሲሆን ሰውን ሁሉ ወደ ዘለአለም ህይወት ከመምራት የበለጠ ደግሞ ምንም መልካም ነገር የለም፣ አማኞች ለዚህ ታላቅ ተልዕኮ ሁልጊዜ የተጋን እንድንሆን ጌታ ይርዳን፣
view more