ወንጌል መንግስትን ያህል ትልቅ ነገር ከጀርባው ያዘለ ታላቅ ሐይል ነው፣ ይህቺ መንግስት ደግሞ በሰማይ ሆና በዚህ ምድር ግዛትዋን የምታሰፋ ስትሆን በመጨራሻው ዘመን የዚች መንግስት መቅረብ ለአለም ሁሉ ይነገራል፣ መንግስቱ ከዚህ አለም ስለአይደለች ማንም የማይጋራት ሁሉን የምትገዛ መንግስትና ዋስትና ያለበት የዘለአለም አምላክ ገዢዋ የሆነ በመልካም ዕንቁ የተመሰለች መንግስት ናት፣ ሃጢያታችንን በመናዘዝ በወንጌሉ አምነን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ሁሉ የላይኛው መንግስት ወራሾች ስለሆንን በምድራዊ ነገር ላለመያዝ መትጋት አለብን፣
view more