ሰው ሸምግሎ አርጅቶ በስራው ሁሉ በእግዚአብሔር ከመባረክ የበለጠ ምንም ነገር የለም፣ ወደዚህ በረከት ለመምጣት ሚስጥሩ መታዘዝ ሲሆን ለመታዘዝ ማመን ያስፈልጋል ለማመን ደግሞ መስማት ያስፈልጋል፣ ከዘለአለም ጥፋት ያዳነንና በክርስቶስ እየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ያስቀመጠን እምላካችን የከፍታውን ስፍራ እንድንይዝ ይወዳል፣ ምንም እንኳን በምድር ብንኖር በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ነንና በላይ ያለውን ለመሻት መትጋት አንዳለብን መፅሐፍ ቅዱሳችን በተደጋጋሚ ያሳስበናል፣ በህይወታችን የምንበረታውና የሰማዩን መንግስት በትጋት የምንጠብቀው ልባችን የተዘጋጀውን ያህል ነው፣
view more