አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ የጌታን መንገድ የተከተለ ሰው ነው፣ አካሄዳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ስናደርግ በእግዚኣብሔር ፊት ቅኖች በሰውም ፊት በደል የማይገኝብን እንሆናለን፣ አካሄዳችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆን የምናዝን የምንምር የዋሆች ጽድቅን የምንራብ ልበ ንጹሀንና የምናስተራርቅ እንሆናለን፣ አካሄዳችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆን የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ እስከ መጨረሻው እንድንዘልቅ ይረዳናል፣
view more