የጌታን ምጽአት ከዘመን ጋራ እንድናስተውል መጽሃፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ ጸሎትም መጸለይ የሚቻለው እግዚአብሔር ዘመኑን ከገለጠበት ከበራልን ነው፣ ዘመኑን ካልተረዳን ጸሎትም አይኖረንም፣ እግዚአብሔር ለህዝቡ ሳይናገር ምንም የሚሆን ነገር ስለሌለ እርሱን ብቻ ከሰማን ሳንናወጥ እግዚአብሔር ያለው እንደሚሆን አውቀን መደረግ የሚገባውን ነገር እያደረግን መሆን የሚገባንን እየሆንን የመጣው ዘመን ሳያሰናክለን ጸንተን መኖር እንችላለን፣ ዘመንን ደግሞ ከእግዚአብሔር ካልሰማን እንዴትና ስለምን እንደምንጸልይ አንረዳም ከእግዚአብሔር ለሰሙ ሰዎች ደግሞ እንቅፋት እንሆናለን
view more