የጸለይንበት ማለት እግዚአብሔር እንካችሁ ብሎ የሰጠን ነገር ማለት ነው፣ የእግዚአብሔር ስጦታ ፍጹም በረከትና መርገም የሌለበት ሲሆን በባህሪው ደግሞ ደግ አባት በመሆኑ የሰጠንን መልሶ አይወስድብንም፣ ልጅን የሚያክል ውብ ነገር ከምጥ በሗላ እንደሚገኝ አንዳንዴ ከውስጣችን የሚወለድ ነገር ካለ እግዚአብሔር እንድናምጥ ያደርገናል፣ በምጥና በስቃይ ውስጥ ስናልፍ በእግዚአብሔር ፊት ጥሩ ባልሆነው ነገር እንዳንያዝ በጥንቃቄ የእግዚአብሔርን ጥሩ ለማወቅ መጸለይና የእርሱን ጥሩ ለማድረግም ሆን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለብን፣
view more