በእግዚአብሔር መታሰብ ውስጥ ያሉ ሶስት ነገሮች ቦታ ሁኔታና ሰዓት ናቸው፣ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሊያገናኘንና በበለጠ ወደ እርሱ ሊያስጠጋን፣ በወሰነው ስፍራ በተለያዩ ሁኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፣ እነኚህ ሁኔታዎች የመታሰቢያችን ምክኒያቶች ናቸው፣ ሁኔታዎችን ለመቀየር መታገል ለውድቀት እራስን ማጋለጥና መከራችንን ማብዛት ነው፣ የሚሻለን ሁኔታዎችን በእግዚአብሔር እይታ እያየናችው በራሱ ጊዜ በማዳን የሚገለጠውን ጌታን ብቻ ተስፋ በማድረግ እርሱን መጠበቅ ነው፣
view more