በህይወት ጉዞ ውስጥ መልካምና በጎ የሀሴትና የደስታ ጊዜዎች እንዳሉ እንዲሁ ደግሞ የምናልፋቸው ብዙ አስጨናቂና አስፈሪ ሁኔታዎች ይኖራሉ:: አናልፍም ያልናቸውን አልፈንና ተሻግረን ዛሬን መድረሳችን ከሚመራንና ካሳለፈን ከእግዚአብሔር የተነሳ ብቻ ነው:: የእግዚአብሔር እኛን የመምራቱ ችሎት ከሚያስጨንቀን ከወጀቡ በማሳለፍ ይገለጣል:: በልጆቹ ላይ ክፉው የክፉውም ማስጨነቅ ስልጣን የለውምና:: ይሁ ደግሞ ለስሙ ክብር ይሆናል::
view more