እግዚአብሔር እርሱ የቃል ኪዳን አምላክ ነው:: ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ህዝብ ያስባል:: የምናልፍበት ማንኛውም ሁኔታ በፊቱ ነው:: በጊዜው ጉብኝት ይሆናል:: በእግዚአብሔር መታሰባችንም በተለየ ሁኔታ ይገለጣል:: የአስበኝ የፀሎት መልስ እውን ይሆናል:: ጨለማው በብርሃን ይለወጣል:: ከውድቀት መነሳት ይሆንል:: ከድካም መበርታት ይሆናል:: ተስፋም ይሞላል::
በህይወታችን ያለው አንዱ ተስፋ እርሱም በእግዚአብሔር የምንታሰብ ሰው መሆናችን ነው::
view more