የእግዚአብሔር ቃል ምን ያህል አቅምና ጉልበት እንዳለው የተረዳው ፣የእምነት ምሳሌ አባታችን አብርሃም ልጁን ለመሰዋት አልራራም። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረን ቃልና እኛ የምናልፍበት መንገድ ፈጽሞ ላይገጣጠም ይችላል ሆኖም ግን የተናገረን እግዚአብሔር ይሁን እንጂ፣ የሌለን ነገር ወደ መኖር የሚያመጣ፣ ቃሉን የማያጥፍ ጌታ፣ በቃሉ ይገኛል፣ ከኛ ጋርም ሆኖ የሚያናውጠንን ወጀብ ጸጥ ያደግልናል። ቃል ካለን፣ ባዶ አንሆንም፣ አንወድቅም፣ አንጠፋም፣የማንሻገረውም ማዕበል አይኖርም።
view more