የቀደመችው ቤተክርስቲያን አንዱ መታወቂያዋ እግዚአብሔርን መፍራት ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ስዎች እግዚአብሔርን በመፍራት እንደከበሩና ብዙዎች ደግሞ እርሱን ባለመፍራት ፍርድን እንደተቀበሉ ያስተምረናል። እግዚአብሔርን በመፍራት የምንኖረውን ኑሮ እውን ለማድረግ፣ ለአባትነቱ የሚገባውን አክብሮት ፣ ልጌትነቱ የሚገባውን ክብር፣ በመስጠትና እንዱሁም ለእርሱ ሀሳብና ትዕዛዝ ምላሽ በመስጠት እንገልጻለን።
እግዚአብሔርን በመፍራት ስንኖር ጌታ ይከብራል፣ እኛም ከተለያየ የሀጢያት ክፋት እንጠበቃለን፣ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖሩትን ወገኖች ልብ ደግሞ እናሳርፋለን።
view more