ደቀመዛሙርቶቹ እርሱን ሲያዩት፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት። መንፈሳዊ አይኖቻችን ተከፍተው፣ ጌታን ካላየን፣ የምንፈልጋቸው ጊዚያዊ ነገሮች፣ ክጌታ እኩል ይሆኑብናል፣ አንዳንዴም ከጌታ በልጠውብን እናገኛቸዋለን። ለአንድ መንፈሳዊ ስው ትልቁ ስጦታው የአይን መከፈት ነው። አይናችን ሲከፈት፣ ሁሉን ለመተውና፣ ጌታችን የሆነውን ክርስቶስን እስከመጨረሻ ለመከተል፣ የሚከፈለውንም ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የተዘጋጀን እንሆናለን።
view more