የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም ፣ የጌታ እየሱስን ስልጣንና ሃይል፣ እንዲሁም የተሰጠንን መሳሪያ አጠቃቀም ማወቅ አለብን። ይኸውም፣ ወገባችንን በእውነት መታጠቅ፥ የጽድቅን ጥሩር መልበስ፥ የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልናጠፉ የምንችልበትን የእምነትን ጋሻ ማንሳት፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ መያዝ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ እየጸለይን፤ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመነን በመጽናት ሁሉ መትጋት የገባናል።
view more