የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተስፋ፣ በክርስቶስ ደም ታጥበን የእግዚአብሔር ልጆች ለሆንን ሁሉ የተሰጠ ተስፋ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፣ አዲስ ስውና ትሁት ያደርገናል፣ ሀይላችንና ሰላማችን፣ አፅናኛችን፣ አስተማሪያችን፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሳስበን ነው። በዚህ ነውጥ በበዛበት አለም ውስጥ፣ ከመቼውም በበለጠ ይህ መንፈስ በሚይስፈልገን ጊዜ፣ ከዚህ ተስፋ ውጪ ብንሆን እጅግ በጣም እንጎዳለን።
view more