የቀደመችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል እውነት የምትመላለስ በፀና መሠረት ላይ የታነፀች ነች:: ይህ ደግሞ ከቃሉ የተነሳ በጌታ ላይ የፀና ህይወት መኖርን ያመለክታል::
በእግዚአብሔር ቃል ሥር የሰደደና የፀና ህይወት ከየአቅጣጫው በሚነፍሰው የአመፅና የክፋት ንፋስ አይናወጥም:: ስለዚህም ነው ወንጌል በብዙ ፈተናና መከራ አልፎ ወደእኛ የደረሰው::
በዚህ መልዕክት ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል እለት እለት በህይወታችን ደግሞም በቤተክርስቲያን ያለውን ስፍራና ፋይዳ እንዲሁም ከእኛ የሚጠበቀው ምን እንደሆነ እንማርበታለን::
view more