ሰው ለሚያውቀው ምህረትን ሊያደርግ ይችላል ያም ቢሆን እንኳን ምህረቱ ውስን ነው። የእግዚአብሔር የአምላካችን ምህረት ግን ለዘለአለም ነው። ደግሞም ምህረቱ በሁኔታዎች ወይም በስሜት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ ቸርነትና ምህረት ባህሪው ነው። በእግዚአብሔር ቤት ለመኖራችን ዋስትና ምህረቱ ነው፣ በዚህ ብዙ ውጣ ውረድና መከራ በበዛበት አለም፣ ወደ ፊት ለመራመድ አቅም የሚሆነን የእርሱን ፍቅር፣ ምህረቱንና በጎነቱን ሁልጊዜ ስናስብ ነው።
view more