እግዚአብሔር በሰው አይምሮ የማይቻል፣ በስርአትና በሕግ የማይንካ ነገርን አልፎ ይነካል ። በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑን በእግዚአብሔር የተነኩና ከቀድሞ ማንንነታቸው የተለወጡ ሰዎች ተጠቅሰውልናል። ሰው ከመለኮት ጋር ከተነካካ የቀድሞውን ማንነቱን መሆን አይችለም። ምህረትን፣ ፍቅርንና ፅድቅን የተለማመደ፣ በብርሀን የሚመላለስና፣ የአሸናፊነት ህይወት ያለው ይሆናል። ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል እየሰማን፣ እያመለክንና እያገለገልን፣ የደከምንበት ወይም ያልተነካንበት ነገር ካለ፣ ይህንን ታላቅ ጌታ እንጠይቀው፦ በመራራት፣ እጁን በድን ወደሆነው ነገራችን ላይ ይዘረጋል።
view more