በራሳችን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ እየጣርን፣ እየወጣንና እየወረድን ብዙ እየደከምን፣ ይሄ ሁሉ ድካማችን ግን ከእርሱ ደስታ ጋር አላገናኘን ይሆን። ኢዮሣፍጥ የተባለ የይሁዳ ንጉሥ አንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር እንደተገኘበት መፅሐፍ ቅዱሳችን የነግረናል። ይህም ነገር እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን ማዘግጀቱ ነው። እግዚአብሔርን የሚያስደስተው፣ የኛ ልጅ መሆን ነው። እኛም ልጅ መሆናችን ከገባን፣ ልጅነታችንን፣ ከአባታችን ጋር ህብረት በማድረግ፣ እርሱን በመውደድና በመታዘዝ፣ በልጅነት ስፍራችን ልንገኝ ይገባናል።
view more