እግዚአብሔር ሂዱ ባለን መንገድ ላይ ከሆንን፣ በተለያየ እቅጣጫ ብዙ የሚያናውጥ ሁኔታ በዙሪያችን ቢከስት እንኳን፣ ፍጥረት ሁሉ የሚታዘዝለት ይሄ ታላቅ ጌታ ብቻችንን እይተወንም። ሂዱ ያለን አምላክ እንደማይተወን በማመን፣ በስልጣኑ ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላካችን፣ የሚናገረንን ቃል ብቻ እየሰማን፣ በዙሪያችን ያለውን ወጀብ ሳይሆን፣ አይኖቻችንን ብርቱ በሆነው አምላክ ላይ ልናደርግ ይገባናል።
view more