ያለ መንፈስ ቅዱስ ህይወትም ሆነ አገልግሎት ድካም ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተነገረለትና፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተወለደው ትልቁ አምላካችንና ጌታችን ወንጌልን መስበክ የጀመረው፣ በሽተኞችን ይፈውስና አጋንንትን ያስወጣ የነበረው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው: በሚያደርገው ነገር ሁሉ ይህ መንፈስ አብሮት ነበር ። ትልቁ ጌታችን በመንፈስ ይህን ካደረገ፣ ለኛ ለደካሞቹ ምን ያህል ይህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያስፈልገን ማሰብ አያዳግተንም። ይህ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የሚሠጠው ፈቃደኛ ለሆኑና ለሚፈልጉት ስለሆነ፣ ዕለት ዕለት ከምንም ነገር በላይ አጥብቀን ልንፈልገውና ልንሞላው የተገባ ነው።
view more