ተለክቶ በተሰጠን በዚህ ዘመናችን በእኛ ህይወት እግዚአብሔር ሊያደርግ ካቀደው ከወሰነው ማንኛውም ነገር ከማድረግ ከመፈፀም የሚያግደው አንዳችም ነገር የለም:: የሚያገኘን ክፋት ደግሞም የምናልፍበት ሁኔታ በእኛ ላይ ያለውን የጌታን ጥበቃ ሊያልፍ ማዴኑንም ሊከለክል አይችልም::
ለትምህርታችን ተፅፏልና በቀደሙት የእምነት አባቶች ህይወት የተገለጠውን የጌታን ማዳን ጥበቃውንም በዚህ መልዕክት በስፋት እንማራለን:: ዛሬም ጌታ የሚታደግ የሚያስመልጥ እንደሆነ እናይበታለን::
view more