የክብርን ወንጌል ሰዎች ሰምተው ወደ ጌታ እንዳይመጡ ከሚዋጋበት መንገድ አንዱ የሰዎችን መንፈሳዊ አይን በማሳወር ጆሮንም በማደንቆር ነው:: በአማኞችም አዕምሮ ክፉ ሀሳብን በመላክ ደግሞም አይኖቻችን በአለም ውበት እንዲሳቡ በማድረግ ይዋጋል:: ይሁን እንጂ በክርስቶስ በስሙ ስልጣንና በፀጋው ጉልበት አሸናፊዎች ነን:: ለጨለማው ገዢ እምቢ እያልን ለጌታ ግን በመገዛትና በመታዘዝ ፈቃዳችንንም ሁሉ ለእርሱ ፈቃድ በማስገዛት ልንመላለስ ያስፈልጋል
view more