የአማኞች በምድር ላይ መኖር የእግዚአብሔርን መንግስት ለማወጅ ነው:: ለማስፋትም ነው:: በዚህ የጨለማው አለም የእግዚአቤሔር መንግስት የምትሰፋው በመውረሰ ነው:: በመማረክ ነው:: ይህም የሚሆነው አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች በፀሎት ሆነው መንግስትህ ትምጣ እያሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በማወጅ ደግሞም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ዝቅ በማለት በትህትና በቅድስናና በፅድቅ በመመላለስ በኑሮ በመስከር ነው::
በዚህ መልዕክት ስለ እግዚአብሔር መንግስት ስርአት ደግሞም በውስጧ እንዴት ባለ ሁኔታ ልንኖር እንደሚገባ በስፋት እንማራለን::
view more